የሰጋጆች ስህተት 04 (ወደ ላይ ማንጋጠጥ/መመልከት) #ሶላት #ኢባዳ #ኢስላም

3 years ago

የሶላት ማእዘናት
ሶላትን የሚመሰርቱ፣ለማድረግ ያለመቻል
ሁኔታ ብቻ ሲቀር በምንም ሁኔታ ሊተው
የማይችሉ፣በማወቅም ሆነ በመዘንጋት ውድቅ
የማይሆኑ የሶላት መሰረታዊ ክፍሎች ናቸው፡፡
1. ንይ’ያህ ማድረግ፡፡
2. በግዴታ ሶላት አቅም እስካለ ድረስ መቆም፡፡
3. የእሕራም ተክቢራ፡፡
4. ፋቲሓን መቅራት፡፡
5. ሩኩዕ፡፡
6. ከሩኩዕ ቀና ብሎ መቆም (እዕትዳል)፡፡
7. በሰባቱ አካላት ሱጁድ መውረድ፡፡
8. በሁለቱ ሱጁዶች መካከል መቀመጥ፡፡
9. ለመጨረሻው ተሸሁድ መቀመጥ፡፡
10. የመጨረሻውን ተሸሁድ መቅራት፡፡
11. በመጨረሻው ተሸሁድ በነቢዩ صلى الله عليه وسلم ላይ ሶላት
ማውረድ፡፡
12. ሰላምታ (ተስሊም)፡፡
13. በሁሉም ማእዘናት ውስጥ የእርጋታ
(ጡመእኒና) መኖር፡፡
14. የማእዘናቱን ቅደም ተከተል መጠበቅ፡፡

ሁለተኛ - የሶላት ግዴታዎች
(ዋጅባት)
የሶላት ግዴታዎች
በመርሳት ሱጁድ የሚካካስና ከተረሳ የሚቀር፡፡
1. በሶላት ክፍሎች መካከል የሚደረጉ የመሸጋገሪያ
ተክቢራዎች፡፡
2. ሩኩዕ ላይ ‹‹ሱብሓነ ረብ’ቢየል ዐዚም›› ማለት፡፡
3. ‹‹ሰምዐል’ሏሁ ልመንሐምደህ›› ማለት፡፡
ለኢማምና ለብቻው ለሚሰግድ ሰው፡፡ ለመእሙም
የተደነገገ አይደለም፡፡
4. ከሩኩዕ ቀና ሲባል ‹‹ረብ’በና ወለከል ሐምዱ››
ማለት፡፡
5. ሱጁድ ውስጥ ‹‹ሱብሓነ ረብ’ቢየል አዕላ››
ማለት፡፡
6. በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ‹‹ረብብ እግፍርሊ››
ማለት፡፡
7. ለመጀመሪያው ተሸሁድ መቀመጥ፡፡
8. የመጀመሪያው ተሸሁድ፡፡

Loading comments...