Premium Only Content

የጨጓራ ባክቴሪያ
#የጨጓራ #ባክቴሪያ
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
⏩ #የጨጓራ ባክቴሪያ ወይም ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ(Helicobacter pylori (H. pylori)) ወደ ሰውነታችን በመግባት የምግብ ትቦ ላይ እና ጨጓራ ውስጥ መኖር የሚችል ነው፡፡ ይህ ባክቴሪያ ሳይታከም ከቆየ አልሰር/ ቁስለት በጨጓራ ላይ እና በትንሹ አንጀት የላይኛው ክፍል ላይ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ አለፈፍ ሲልም ካንሰርንም ሊያስከትል ይችላል፡፡
🔹 በጨጓራ ባክቴሪያ መያዝ በብዙዎች ላይ የሚያጋጥም የተለመደ በሽታ ቢሆንም ባክቴሪያው አንዳንድ ሰዎች ላይ ምንም ምልክት የማያሳይ፣ የቁስለት ሁኔታም የማይፈጥር ቢሆንም ብዙዎችን ግን ለከፍተኛ ለሕመም ይዳርጋል፡፡
⏩ #ባክቴሪው #እንዴት #ህመም #ይፈጥራል?
🔹 የጨጓራ ባክቴሪያ ወደ ሰውነት ከገባ በኋላ በጨጓራ ውስጣዊ አካል ላይ ጥቃት በመፈፀም ጨጓራችንን ተጋላጭ ያደርገዋል፤ ምክንያቱም ጨጓራችን ምግብ ለመፍጨት አሲድ ይጠቀማል፡፡ ይህ አሲድ በጨጓራ አካል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሚያደርገው የጨጓራ ውስጣዊ አካል ነው፡፡ ይህ አካል ከተሸረሸረ ጨጓራችን ለአሲዱ የተጋለጠ ስለሚሆን ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ጉዳቱ የደም መፍሰስ ጨምሮ አካሉ እንዲቆስል፣ እንዲሁም የበላነው ምግብ እንዳይፈጭና እንዳይረጋ ሊያደርግ ይችላል፡፡
⏩ #ይህ #ባክቴሪያ #ከየት #ሊያገኘን #ይችላል?
🔹 የጨጓራ ባክቴሪያ ከምንበላው ምግብ፣ ከምንጠጣው ውኃና ከምንጠቀማቸው በባክቴሪው ከተበከሉ ቁሶች ሊያገኘን ይችላል፡፡ በሽታው አብዛኛውን ጊዜ ፅዳት በሚጎድልባቸው አካባቢዎች የሚከሰት ሲሆን ባክቴሪያው በምራቅ ንክኪና ባክቴሪያው ካለበት ሰው ጋር በሚኖር የፈሳሽ ንክኪ ሊተላለፍብን ይችላል፡፡
⏩ #የጨጓራ #ባክቴሪያ #ምልክቶች #ምንድን #ናቸው?
🔹 የሆድ መነፋት፤
🔹 ግሳት፤
🔹 የረሃብ ስሜት አለመሰማት፤
🔹 ማቅለሽለሽ፤
🔹 ማስመለስ፤
🔹 ቁስለት ከተፈጠረብን በሆዳችን የላይኛው ክፍል የማቃጠልና የመደንዘዝ ስሜት፤
🔹 ያለምክንያት ��ብደት መቀነስ ሊታዩ ይችላሉ፡፡
⏩ #መቼ #ወደ #ህክምና #መሄድ #ይኖርብናል?
🔹 የሰገራ መጥቆርና ደም መቀላቀል ካለ፣
🔹 ለመተንፈስ መቸገር ካጋጠመን፣
🔹 ያለስራ የመልፈስፈስና የድካም ስሜት ከተጫነን፣
🔹 የቆዳ መገርጣትና ራስን የመሳት ሁኔታ ከታየብን፣
🔹 የተፈጨ ቡና የመሰለ ነገር የሚያስመልሰን ከሆነ፣
🔹 ከባድ የሆድ ህመም ካለን የጨጓራ ባክቴሪያ ሊሆን ስለሚችል መታየት አለብን፡፡
⏩ #ምርመራ
🔹 የኋላ ታሪክን በመጠየቅ
🔹 የትንፋሽ ምርመራ
🔹 የኢንዶስኮፒ ምርመራ
⏩ #ሕክምና
🔹 ጸረ - በክቴሪያ መድኃኒቶች
🔹 በጨጓራ ውስጥ አሲድ የሚረጩትን ጥቃቅን ቧንቧዎች በመዝጋት አሲድ የሚቀንሱ መድኃኒቶችን
🔹 የአመጋገብ ስርአት ማስተካከለል ይካተቱበታል፡፡
-
LIVE
StoneMountain64
2 hours agoBF6 Full Release Gameplay Review - I have been playing EARLY
172 watching -
1:28:11
Sean Unpaved
2 hours agoSnap Counts & Showdowns: Hunter's Usage, CFB Fire, & Playoff Baseball Bonanza
18.4K1 -
56:09
Steven Crowder
5 hours agoBlack Fatigue is Real and I Told Them Why | Black & White on the Gray Issues
253K1.04K -
Simply Bitcoin
2 hours ago $0.33 earnedLEAKED CONVERSATION: US SECRET Bitcoin Plan EXPOSED?! | EP 1350
2621 -
3:36:42
Barry Cunningham
14 hours agoBREAKING NEWS: PRESIDENT TRUMP HOSTS FULL CABINET MEETING!
25.5K8 -
1:59:05
The Charlie Kirk Show
2 hours agoTurning Point Halftime + Antifa Panel Aftermath + Right-Wing Taylor Swift? |Patrick, Cuomo|10.9.2025
61.8K25 -
27:46
Jasmin Laine
3 hours agoCBC TURNS On Carney After Trump HUMILIATES Him–Poilievre’s Response Goes Viral
5.62K6 -
4:27:44
Right Side Broadcasting Network
6 hours agoLIVE REPLAY: President Trump Hosts a Cabinet Meeting - 10/9/25
110K44 -
1:13:52
Mark Kaye
2 hours ago🔴 Schumer BUSTED Celebrating Democrat Shutdown!
3.76K4 -
1:00:33
Timcast
3 hours agoTrump To Declare Antifa FOREIGN Terrorist Org, Antifa Leaders FLEE Country
139K101