ልዩ ምርቃት(አፋብኃ ምስራቅ አማራ ሚኒሊክ ዕዝ

12 days ago
85

መብረቅ ክፍለጦር ለስድስት ወራቶት ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ::

ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለጦር ለስድስት ወራቶች ያሰለጠናቸውን በርካታ ቁጥር ያላቸው ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች ህዳር 14/2018 ዓ.ም በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል::

ምኒልክ ዕዝ አደረጃጀቱን በማዘመን የህልውና ትግሉን አጠናክሮ እየታገለ ያለ ሲሆን ሰራዊቱን በመደበኛ እና በልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች ደረጃ በሰው ሃይል እና በጦር መሳሪያ ማጠናከሩን በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራበት ይገኛል::

መብረቅ ክፍለጦር ባለፉት ጊዜያት ተደጋጋሚ ስልጠናዎችን በመስጠት ሰራዊት እያስመረቀ ራሱን በሰው ሃይል አጠናክሮ የመጣ ሲሆን ዛሬም በርካታ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎችን በማስመረቅ የቀደመ ተግባሩን እያስቀጠለ ይገኛል::

"እየሰለጠንን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!"

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ስልጠና መምሪያ ክፍል
ህዳር 15/2018 ዓ.ም

Loading comments...